የሃይማኖቱን ሕግጋት እንዴት አውቃለሁ?

የሃይማኖቱን ሕግጋት እንዴት አውቃለሁ?

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ይላሉ «እስልምና በአምስት ነገሮች ላይ ተገንብቷል፡፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፣ ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር፣ ሰላትን መስገድ፣ ዘካ መስጠት፣ሐጅ ማድረግና ረመዷንን መፆም ናቸው፡፡» (አል-ቡኻሪ፡ 8 ሙስሊም፡16)

አምስቱ የእስልምና መሠረቶች፡-

የዚህ ዓለም ታላቅ ፀጋ

ኃያሉ አላህ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ፀጋዎችን ለሰው ዘር አጎናፅፏል፡፡ ሁላችንም እነዚህን የአላህ ፀጋና ትሩፋቶች ከማጣጣም ለአፍታም ተቆጥበን አናውቅም፡፡ ከጎደሎ ባህሪያት የጠራው ጌታ ብዙዎች ያጡትን የማየትና የመስማት ታላቅ ፀጋን ችሮናል፡፡ አዕምሮን፣ ጤናን፣ ገንዘብን፣ ቤተሰብን ያለክፍያ ሰጥቶናል፡፡ ከዚህም አልፎ ተርፎ ፍጥረተ-ዓለሙ ሁሉ እኛን ያገለግል ዘንድ ገርቶናል፡፡ ፀሐዩ፣ ሰማዩ፣ መሬቱ፣ ፍጥረታቱ ሁሉ የእኛ አገልጋይ ተደርገዋል፡፡ «የአላህንም ፀጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፤ አላህ በእርግጥ መሐሪ አዛኝ ነውና፡፡» /አል-ነሕ፡18/

Read More የዚህ ዓለም ታላቅ ፀጋ