
የሸሪዓ ሕግጋት፡-
በሸሪዓ ሕግጋት መሠረት የአንድ ሰው ንግግርም ሆነ ተግባር ከአምሰት ማዕቀፎች ሊወጣ አይችልም፡፡
አልዋጂብ (ግዴታ) |
የግዴታ ተግባር ማለት አላህ ያዘዘው፣ ተግባሪው ምንዳ የሚያገኝበትና ከመተግበር የታቀበው ደግሞ የሚቀጣበት ተግባር ማለት ነው፡፡ አምስቱ ሶላቶችና የረመዷን ፆምን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ |
ሐራም (ክልክል) |
ክልክል ተግባር ማለት አላህ የከለከለው፣ ከመተግበር የታቀበው ምንዳ የሚያገኝበትና የተገበረው ደግሞ የሚቀጣበት ተግባር ማለት ነው፡፡ ዝሙትና አስካሪ መጠጥን በምሳሌነት ማውሳት ይቻላል፡፡ |
አስሱና ወአል ሙስተሐብ (ተወዳጅ ተግባር) |
ይህ ደግሞ ይተገበር ዘንድ ኢስላም ያበረታታው፣ ተግባሪው ምንዳ የሚያገኝበትና ከመተግበር የታቀበው ደግሞ የማይቀጣበት ተግባር ማለት ነው፡፡ ሰዎች ጥሩ የሆነን ፈገግታ ማሳየት፣ ቀድሞ ሰላምታ ማቅረብና ከመንገድ ላይ ቆሻሻን ማስወገድ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ |
የሚጠላ (ከርሃ) ነገር ማለት |
የእስልምና ሃይማኖት አንዳይደረግ ያበረታታው ተግባር ማለት ሲሆን ይህን ተግባር ከማድረግ በመቆጠብ ምንዳ የሚገኝ ሲሆን መተግበሩ ግን ለቅጣት አይዳርግም፡፡ በሶላት ውስጥ ጣትን እያነቃነቁ መጫወት ከዚህ የተጠላ «መክሩህ» ተግባር ውሰጥ ሊመደብ ይችላል፡፡ |
የተፈቀደ (ሙባሕ) ማለት ደግሞ |
መተግበሩም ሆነ መቆጠቡ፥ ከልካይና አዛዥ ከሆነ የህግ (ሸሪዓ) መርህ ጋር ግንኙነት የሌለው ክንውን ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ መሠረታዊ በሆነ መልኩ መብላት፣ መጠጣት፣ መናገር ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ |