“ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” የምንለው ለምንድ ነው?
“ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” የሚለው ቃል ትርጉም
“ከአላህ በስተቀር በእውነተ የሚመለክ አምላክ የለም” የሚለው ቃል መሠረቶች

ወደ ተለያዩ ህዝቦች የተላኩ ነቢያት በሙሉ ይዘው በተነሱት ተልእኮ ውስጥ “አላህ ያለማንም ተጋሪ በብቸኝነት መመለክ ይኖርበታል፡፡ ከርሱ ውጪ ሌላን በማምለክ ሊካድ አይገባውም” የሚል ሙሉ ስምምነት አለ፡፡
ይህ ዕውነታ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፡፡ ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው፡፡” የሚለውን ቃል ያንፀባርቃል፡፡ አንድ ሰው ወደ አላህ ሃይማኖት ሊገባ የሚችለው በዚህ ቃል አማካኝነት ነው፡፡