- ሐደስ፡ ማለት ምናባዊ የሆነ፣ ሰው ከርሱ ከመጥራቱ በፊት ሠላት መስገድን የሚከለክል ነገር ነው፡፡ እንደ ነጃሳ በግልፅ የሚነካ ነገር አይደለም፡፡
- ሐደስ ከአንድ ሙስሊም ላይ የሚወገደው ሊያጠራ በሚችል ውሃ ወዱእ ሲያደርግ ወይም ገላውን ሲታጠብ ነው፡፡ ሊያጠራ የሚችል ውሃ የሚባለው፣ ነጃሳ ያልተቀላቀለበት ውሃ፣ ወይም ነጃሳ ነክቶት፣ መልኩን ወይም ጣዕሙን ወይም ሽታውን ያልቀየረው ውሃ ነው፡፡
- ሐደስ በሁለት ይከፈላል፡፡
-
1
አንድ ሰው እርሱን ከላዩ ላይ ለማስወገድ የግድ ውዱእ ሊያደርግ የሚገባው ዓይነት ሲሆን እሱም ትንሹ ሐደስ ይባላል፡፡
-
2
አንድ ሰው እርሱን ከላዩ ላይ ለማስወገድ የግድ በውሃ ገላውን ሙሉ በሙሉ በማደረስ መታጠብ ያለበት ዓይነት ሲሆን ትልቁ ሐደስ በመባል ይጠራል፡፡
-
ትንሹ ሐደስና ውዱ
አንድ ሙስሊም ምናባዊ ጽዱዕነቱን አጥቶ ውዱእ ማድረግ የግድ የሚሆንበት ከሚከተሉት ነገሮች አንዱ በሚከሰበት ጊዜ ነው፡፡
1
ሽንት፣ ዓይነምድርና ማንኛውም ከሁለቱ መጸዳጃ ብልቶች የሚወጣ ንፋስና መሰል ነገሮች ከወጡ፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ጽዱዕነትን የሚያፈርሱ ነገሮችን ሲዘክር፡- «ወይንም ከናንተ አንዱ ከዓይነምድር ቢመጣ» ብሏል፡፡ (ኒሳእ 43) ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) በሠላት ውስጥ ሆኖ ሐደስ እንደተከሰተበት የተጠራጠረን ሰው በማስመልከት፡- «ድምጽ እስካልሰማ ወይም ሽታ እስካለገኘ ድረስ አቋርጦ አይሂድ!» ብለዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 175/ ሙስሊም 361)
2
ያለግርዶ በስሜት ብልትን መንካት፡ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ)፡- «ብልቱን የነካ ሰው ወዱእ ያድርግ» ብለዋል፡፡ (አቡ ዳውድ 181)
3
የግመል ስጋ መብላት፡ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ)፣ «የግመል ስጋን በመብላቴ ውዱእ ላድርግን?» የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው፣ «አዎን» በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡ (ሙስሊም 360)
4
አእምሮ በእቅልፍ ወይም በአእምሮ ህመም ወይም በስካር መሳት