የንጽህና መሰረታዊ ትርጉም፡- መጥራት፣ መጽዳት ወይም መወልወል ነው፡፡
አላህ(ሱ.ወ) አንድ ሙስሊም ላዩንም ውስጡንም እንዲያጠራ አዞታል፡፡
ላዩን ግልጽ ከሆኑ እርም ነገሮች፣እንዲሁም ከቆሻሻና ፀያፍ ነገሮች፣ ውስጡን ደግሞ ከማጋራት(ሺርክ) እና፣ እንደ ምቀኝኘት፣ ኩራትና ቂም ከመሳሰሉ የቀልብ በሽታዎች እንዲያጸዳ አዞታል፡፡ ይህን ከፈፀመ፣ የአላህን ውዴታ ይጎናጸፋል፡፡ አላህ(ሱ.ወ)፡-«አላህ (ከኀጢአት) ተመላሾችን ይወዳል፡፡ ተጥራሪዎችንም ይወዳል፡፡» ይላል፡፡ (አል በቀራ 222)
አላህ(ሱ.ወ) ሠላት ከመስገድ በፊት ከቆሻሻዎች መጥራትን አዟል፡፡ ይህ፣ ሠላት ከአላህ ጋር የመገነኛና የመነጋገሪያ መንገድ በመሆኗ ነው፡፡ በተለምዶ እንደሚታወቀው አንድ ሰው ከአንድ ንጉሥ ወይም መሪ ጋር በሚገናኝበት ጊዜ ጸዱዕ ሆኖና የሚያምር ልብሱን ለብሶ ነው፡፡ ታዲያ የንጉሦች ንጉሥ የሆነው ኃያሉ አምላክ ጋር የሚገናኝስ እንዴት ሊሆን ይገባል?
አላህ(ሱ.ወ) አንድ ሙስሊም ሠላት ለመስገድ፣ ቁርኣን ለመንካት ወይም በተከበረው ካዕባ ዙሪያ ለመዞር በሚፈልግበት ጊዜ በኢስላማዊው ሕግ የተደነገገን ልዩና እራሱን የቻለ የመፀዳዳት ዓይነትን በቅድሚያ እንዲያከናውን ግዴታ አዘል ትእዛዝን አዞታል፡፡ በበርካታ ስፍራዎች ላይ ደግሞ ይህንኑ እንዲፈፅም በውዴታ ግዴታ (ሙስተሐብ) መልኩ አበረታቷል፡፡ ከነኚህ ስፍራዎች መካከል፣ በእጅ ሳይነካ በቃል ቁርኣንን በሚያነብ ጊዜ፣ ዱዓ ሲያደርግ፣ ሲተኛ፣ እና ወዘተ…
- አንድ ሙስሊም ለመስገድ ሲፈልግ ከሁለት ነገሮች መጥራት ይገባዋል፡፡
-
1
ከነጃሳ(ከግልፅ ቆሻሻ)
-
-
2
ከሐደስ(ምናባዊ ቆሻሻ)
-

አላህ(ሱ.ወ)፣ ሙስሊም ወስጡን ከማጋራትና ከቀልብ በሽታዎች ላዩን ደግሞ ከእርምና ቆሻሻ ነገሮች እንዲያጸዳ አዟል፡፡