
ኢስላም ሠላት በህብረት ወይም በጀመዓ እንዲፈፀም አዟል፡፡ ለሙስሊሞች መገናኛና መሰባሰቢያ መንገድ ይሆን ዘንድም በመስጂድ ውስጥ እንዲፈፀም አበረታቷል፡፡ ይህን በማድረግ፣በመካከላቸው ወንድማማችነትና ፍቅር ይጨምራል፡፡ ኢስላም የጀመዓ ሠላትን አንድ ሰው ለብቻው ከሚሰግደው ሰላት በብዙ ደረጃዎች የሚበልጥ አድርጎታል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- «አንድ ሰው በጀመዓ የሚሰግደው ሠላት በነጠላ ለብቻ ከሚሰገደው ሠላት በሃያ ሰባት ደረጃ ይበልጣል፡፡» ብለዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 619/ ሙስሊም 650/ አህመድ 5921)
ሠላት በማንኛውም ስፍራ ቢሰገድ ትክክለኛ ነው፡፡ ይህም የአላህ እዝነት መገለጫ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- «ምድር መስገጃና ንጹህ ተደርጋልኛለች፤ከህዝቦቼ፣ ማንም ሰው ሠላት ከደረሰበት፣ በደረሰበት ስፍራ ይስገድ» ብለዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 328/ ሙስሊም 521)
የሠላት ቦታ ይዘት
ኢስላም፣ ሠላት የሚሰገድበት ቦታ ንጹህ እንዲሆን በመስፈርትነት አስቀምጧል። አላህ (ሱ.ወ)፡- «ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም፣ ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡» ይላል፡፡ (አል በቀራ 125) የነገሮች መስረት ንጹህ ነው፤ ነጃሳ ደግሞ ባዕድ/መጤ ነው፡፡ ስለሆነም፣ ነጃሳ ያለበት መሆኑን እርግጠኛ ባልሆንክበት ነገር ላይ ንጹህነትን ትወስናለህ፡፡ በመስገጃ ወይም ሰሌን ላይ እንጂ አለመስገድ የሚወደድ ተግባር አይደለም፡፡
ልንከተላቸው የሚገቡ በርካታ ስርዓተ ደንቡች አሉ፡፡ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
1
በመስገጃ ስፍራ ላይ ሰዎችን አለማስቸገር፡፡ ለምሳሌ፡የመተላለፊያ መንገድ ላይ መስገድ፣ እንዲሁም ግፊያና መጨናነቅን በሰዎች ላይ የሚፈጥር ስፍራ ላይ መቆም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሰዎችን ማስቸገርና በነሱ ላይ ጉዳት ማድረስን ሲከለክሉ፡- «መጉዳትም መጎዳትም (በኢስላም) ቦታ የለውም፡፡» ብለዋል፡፡ (ኢብኑ ማጃህ 2340/ አህመድ 2865)
2
በመስገጃ ቦታ ላይ፣እንደ ስዕል፣ ከፍ ያለ ድምጽና ሙዚቃ ያለ፣ ሰጋጅን የሚረብሽና ትኩረቱን የሚበትን ነገር መኖር የለበትም፡፡
3
የመስገጃው ስፍራ ለሹፈትና ለፊዝ የሚያጋልጥ መሆን የለበትም፡፡ ለምሳሌ፡ ሰካራሞች በተሰበሰቡበት ወይም ጽንፈኞች በሚያዘወትሩበት ስፍራና በመሳሰሉት ቦታዎች፣መስገጃ መሆን የለባቸውም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የካሃዲያንን አማልክት መሳደብን የከለከለው እነሱ ባለማወቅ አላህን እንዳይሰድቡ ለመከላከል ሲል ነው፡፡ እንዲህም ይላል፡- «እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚግገዟቸውን (ጣዖታት)አትስደቡ፤ ድንበርን በማለፍ ያለ ዕውቀት አላህን ይሰድባሉና፡፡» (አል አንዓም 108)
4
የመስገጃ ቦታ፣ እንደ ዳንስና ጭፈራ ቤት ያለ፣ አላህን ለማመፅ የተዘጋጀ መሆን የለበትም፡፡ በዚህ መሰሉ ስፍራ ሠላት መስገድ የተጠላ ነው፡፡


- በመስጂድ ውስጥ ከጀመዓ ጋር መስገድ ትችላለህን?
-
አዎን
አዎ፡ ሠላትን በጀመዓ መስገድ በወንድ ላይ የጠበቀ ግዴታ ነው፡፡ ከስራዎች ሁሉ ትልቁና አላህ ዘንድ እጅግ የላቀ ነው፡፡ በጀመዓ መስገድ ለሴቶችም ይፈቀዳል፡፡
-
አይቻልም(በፍፁም)
በመስጂድ ውስጥ መስገድ ካልቻልክ ከሱ ሌላ ያሉ ቦታዎች ነጃሳ ናቸውን?
-
አዎን
በነጃሳ ቦታ ላይ መስገድ የተከለከለ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ለሠላት ጽዱዕ እንድንሆን አዞናል፡፡
-
አይቻልም(በፍፁም)
ቦታው ነጃሳ ባይሆንም ሰዎችን የሚያስቸግር ቦታ ላይ መስገድ ይፈቀዳል? ለምሳሌ መተላለፊያ መንገዳቸው ቢሆን?
-
አዎን
ሰዎችን ማስቸገርና ለመስገድ እንኳን ቢሆን በነርሱ ላይ መጨናነቅን መፍጠር ክልክል ነው፡፡ ሌላ ቦታ ልትመርጥና ልትቀይር ይገባል፡፡
-
አይቻልም(በፍፁም)
እንደ ፎቶና ከፍተኛ ድምፅ የመሰሉ ከሠላትህ የሚያስተጓጉሉ ነገሮች ባሉበት ቦታስ?
-
አዎን
ሰጋጅን ከሚረብሹና ሠላቱን ከሚያስተጓጉሉ ነገሮች ሁሉ መራቅ ያስፈልጋል፡፡
-
አይቻልም(በፍፁም)
ይህ ህዝብ (የነቢዩ ኡማህ) ከተቸረው ልዩ ነገር መሐከል በምድር ላይ በየትም ስፍራ ቢሰገድ ሠላቱ ተቀባይነት ያለው መሆኑ ነው፡፡
-
-
-
-