በምግብና መጠጥ ዙሪያ ያሉ መሰረታዊ መመሪያዎች

በምግብና መጠጥ ዙሪያ ያሉ መሰረታዊ መመሪያዎች


ምግቦችንና መጠጦችን በተመለከት ያለው መሰረታዊ መመሪያ፡ የሰው ልጅን በጤናው፣ በስነ ምግባሩና በሃይማኖቱ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ የሆኑ፣ በክልክለነታቸው ለብቻ ተነጥለው የተጠቀሱት ነገሮች ሲቀሩ ሌሎቹ ሁሉ የተፈቀዱ መሆናቸውን የሚናገር ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እርም ካደረጋቸው ነገሮች በስተቀር በምድር ላይ ያሉ ነገሮችን ሁሉ ለሰው ልጆች የፈጠረላቸው መሆኑ አላህ በሰው ልጅ ላይ ከዋለው ውለታ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለናንተ የፈጠረ ነው፡፡›› (አል በቀራ 29)