
አዛን በአላህ ዘንድ ከላቁ ተግባራት መካከል እንድ ነው።
አላህ ለሙስሊሞች አዛን ያደረገው ሰዎችን ወደ ሰላት ለመጥራትና የሰላት ወቅት መግባቱን እንዲሁም የሰላቱን መጀመር ማሳወቂያ ይሆን ዘንድ ነው። ሙስሊሞች ለሰላት እየተጠራሩ ይሰባሰቡ ነበር። ግን አንድ ለሁሉ የሚጠራ አልነበረም አንዳንዶች የክርስቲያኖችን መሰል ደውል አድርጉ ሲሉ ተወሰኑት ደግሞ
እንደ አይሁዳዊያን ቀንድ ይሁን አለ ዑመር ወይም ለሰላት የሚጣራ ሰው አድርጉ አሉ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንደህ አሉ፦‹‹ ቢላል ሆይ! ተነስና ለሰላት ጥሪ አድርግ።››(ቡኻሪ 579 ሙስሊም377)
የአዛንና የኢቃም መገለጫ
- በአዛንና በኢቃም ስነ- ስርዓት በግለሰብ ሳይሆን በቡድን ላይ ግዴታ ነው። አውቀው የተውት ከሆነ ሃጢአት ኖሮባቸውም ቢሆን ሰላታቸው ትክክል ነው።
- አዛን ለማድረግ በመልካምና በሚሰማ ድምጽ ሆኖ ሰዎች ሰላት እንዲመጡ የሚጣራ መሆን አለበት
- ለአዛንና ለኢቃም የተለያዩና የተረጋገጡ አኳኋኖች ከነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ተዘግበዋል።
አዛን 1አላ…ሁ አክበር፣ አላ…ሁ አክበር፤ አላ…ሁ አክበር አ…ላሁ አክበር! 2አሽሐዱ አን ላ..ኢላ..ሃ ኢለላ…ህ፤አሽሐዱ አን ላ..ኢላ..ሃ ኢለላ...ህ! 3አሽሐዱ አነ ሙሐመደን ረሱ…ሉላ…ህ፤ አሽሐዱ አነ ሙሐመደን ረሱ…ሉላ…ህ! 4ሐይየ ዐለ ሠላ…ህ፤ ሐይየ ዐለ ሠላ…ህ! 5ሐይየ ዐለልፈላ…ሕ፤ ሐይየ ዐለልፈላ…ሕ! 6አላ…ሁ አክበር አላ…ሁ አክበር 7ላ..ኢላ…ሃ ኢለላ….ህ! |
ኢቃም (የሠላት መጀመሪያ ጥሪ) 1አላ…ሁ አክበር፣ አላ…ሁ አክበር! 2አሽሐዱ አን ላ..ኢላ..ሃ ኢለላ...ህ! 3አሽሐዱ አነ ሙሐመደን ረሱ…ሉላ…ህ! 4ሐይየ ዐለ ሠላ…ህ! 5ሐይየ ዐለልፈላ…ሕ! 6ቀድ ቃመቲ ሠላ…ህ ቀድ ቃመቲ ሠላ…ህ! 7አላ…ሁ አክበር፣ አላ…ሁ አክበር! 8ላ..ኢላ…ሃ ኢለላ….ህ! |
ሙኣዚኑን ተከትሎ መድገም
አዛን ለሰማ ሰው፣ ሙኣዚኑን ተከትሎ እርሱ የሚለውን በሙሉ መልሶ ማለት ይወደዳል፡፡ ሙኣዚኑ ‹‹ሐይየ ዐለሠላ..ህ›› እና ‹‹ሐይየ ዐለልፈላ…ሕ›› በሚል ጊዜ ግን፣ ‹‹ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐሊዪል ዐዚም›› ማለት አለበት፡፡
በመቀጠልም፣ ‹‹አላሁም ረበ ሃዚሂ ዳዕወቲታማ ወሠላቲል ቃኢማ ኣቲ ሙሐመደኒል ወሲ..ለተ ወል ፈዲ..ለተ ወብዐስሁል መቃመል መሕሙደኒ ለዚ ወዐድተሁ›› ይላል፡፡

አንድ ሙስሊም ወደ መስጂድ በተራመደው እርምጃ ልክ አላህ (ሱ.ወ) ምንዳን ይከፍለዋል፡፡