የሠላት ማዕዘናት ግዴታዎች

የሠላት ማዕዘናት ግዴታዎች


የሠላት ማዕዘናት የሚባሉት የሠላት ዋና ዋና ክፍሎች ሲሆኑ ታውቆም ሆነ በመርሳት ከተተዉ ሠላት የሚበላሽባቸው ነገሮች ናቸው፡፡


እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡

ተክቢረቱል ኢሕራም (የመግቢያ ተክቢራ ወይም ‹‹አላሁ አክበር‹‹) • መቆም ለሚችል ሰው መቆም • ከተከታይ ወይም ማእሙም በስተቀር ፋቲሐን ማንበብ፤ • ሩኩዕ፤ • ከሩኩዕ ቀና ማለት፤ • ሱጁድ፤ • በሁለት ሱጁዶች መሐከል መቀመጥ፤ • የመጨረሻው ተሸሁድ፤ • ለመጨረሻው ተሸሁድ መቀመጥ፤ • መረጋጋት ወይም ጡመእኒና እና ማሰላመት ናቸው


ሰላት ግዴታዎች ማለት በሰላት ውስጥ ግዴታ የሆኑ አካላት ማለት ሲሆን እነዚህ ግዴታዎች ቢሆን ተብሎ ከተተው ሰላቱ ይበላሻል። ነገር ግን አንድ ሰው ረስቶ ወይም ዘንግቶ ከተዋቸው የጐደለውን ለመሙላት የመርሳት ሱጁድ የመውረድ ግዴታ አለበት። ይህም ወደፊት በሚወጣው ርዕስ የምንመለከተው ይሆናል።


የሰላት ግዴታዎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡

ከተክቢረተል ኢሕራም ውጭ ያሉት ሁሉም ተክቢራዎች፤ • ሩኩዕ ላይ እያሉ አንድ ጊዜ ‹‹ሱብሐነረቢየል ዐዚም›› ማለት፤ • ብቻውን ለሚሰግድና ኢማም ሆኖ ለሚያሰግድ ‹‹ሰሚዐላሁ ሊመን ሐሚደሁ›› ማለት፤ • ለሁሉም ሰጋጅ ‹‹ረበና ወለከልሐምዱ›› ማለት፤ • ሱጁድ ውስጥ አንድ ጊዜ ‹‹ሱብሐነ ረቢየል አዕላ›› ማለት፤ • በሁለቱ ሱጁዶች መሐከል ሲቀመጡ አንድ ጊዜ ‹‹ረቢግፊርሊ›› ማለት፤ እና • የመጀመሪያው ተሸሁድ፤ ናቸው፡፡ እነኚህ ግዴታዎች በመርሳት ምክንያት ከተተዉ ግዴታነታቸው ይቀራል፡፡ እነርሱም የእርሳና ሱጁድ ወይም ሱጁደ ሰህው በማድረግ ይጠገናሉ፡፡


የሠላት ውስጥ ሱናዎች፡ ማንኛውም የሠላት ማዕዘን ወይም ግዴታ ውስጥ የማይመደብ ንግግርም ሆነ ተግባር የሠላት ውስጥ ሱና ይባላል፡፡ ሠላትን የሚያስውብና የሚያሟላ ነው፡፡ በመሆኑም እርሱን በዘውታሪነት መፈፀም ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን እርሱን በመተዉ ሠላት አይበላሽም፡፡


ሱጁደ ሰህው

ሱጁደ ሰህው፣ ሁለት ሱጁዶችን ማድረግ ሲሆን በሠላት ውስጥ ለሚከሰቱ ጉድለቶችና ክፍተቶች ማካካሻና መጠገኛነት የተደነገገ ነው፡፡


ሱጁደ ሰህው ማድረግ የሚፈቀደው መቼ ነው?

በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ሱጁደ ሰህው ይደረጋል፡

1

አንድ ሰጋጅ በመርሳትና በስህተት ምክንያት በሠላቱ ውስጥ ተጨማሪ ሩኩዕን ወይም ሱጁዱን ወይም መቆም ወይም መቀመጥን ከጨመረ ሰጅደተ ሰህው ይሰግዳል፡፡

2

ከሠላት ማዕዘናት መካከል አንዱን ማዕዘን ካጎደላ፣ ያንን ያጎደለውን ማዕዘን ያሟላና በሠላቱ ማብቂያ ላይ ሰጅደተ ሰህው ይሰግዳል፡፡

3

እንደ ተሸሁደል አወል(የመጀመሪያው መቀመጥ) ዓይነት ከሠላት ግዴታዎች መካከል አንዱን ረስቶ ከተወ ሰጅደተ ሰህው ይሰግዳል፡፡

4

የሰገዳቸውን የረከዓት ቁጥር ከተጠራጠረ፣ መጀመሪያ እርግጠኛ የሆነውን፣አነስተኛውን ቁጥር ይይዝና ካሟላ በኋላ ሰጅደተ ሰህው ይሰግዳል፡፡


የአሰጋገዱ ዓይነት፡ በመደበኛ ሠላቱ ውስጥ እንዳለው ሱጁድና መቀመጥ ዓይነት፣ በሱጁዶቹ መሐከል የሚቀመጥ ሆኖ ሁለት ሱጁዶችን ይሰግዳል፡፡


ሱጁድ የማድረጊያው ጊዜ፡ ሱጁደ ሰህው ሁለት ጊዜዎች አሉት፤ ሰጋጁ ከሁለቱ በአንዱ በፈለግው ጊዜ ሊሰግደው ይችላል፡፡

  • ከመጨረሻው ተሸሁድ በኋላ ይሰግዳትና ከዚያም ያሰላምታል፡፡
  • ሠላቱን በሰላምታ ካሰናበተ በኋላ ሁለት ሱጁዶችን ስግዶ፣ ለሁለተኛ ጊዜ በሰላምታ ያሰናብታል፡፡


ሠላትን የሚያበላሹ ነገሮች


1

ሠላት፣ አንድ ሰጋጅ መተግበር የሚችለው ሆኖ፣ ሲታወቀውም ይሁን በስህተት ማዕዘንን ወይም የሠላት መስፈርትን ከተወ ሠላቱ ትበላሻለች፡፡

2

ሲታወቀው ከሠላት ግዴታዎች መካከል አንዱን ግዴታ ከተወ ትበላሻለች፡፡

3

ሲታወቀው ከተናገረ ትበላሻለች፡፡

4

ሠላት ድምጽ ባለው ሳቅ፣ በማሽካከት ትበላሻለች፡፡

5

በማያስገድዱ ሁኔታዎች ውስጥ በሚደረጉ ተከታታይና በርካት በሆኑ እንቅስቃሴዎች ትበላሻለች፡፡


በሠላት ውስጥ የተጠሉ ነገሮች፡፡


የአንድ ሰጋጅ ሰላት በሚኖረው የአላህ ፍራቻና ከሰላት ከሚያዘናጉ ነገሮች መራቁ ምንዳውና ደረጃዎቹ ላቀ እንዲሆን ያደርገዋል።

እነኚህ ነገሮች፣ የሠላትን ምንዳ የሚቀንሱ፣ ለሠላት መተናነስን የሚያጠፉ፣ እና የሠላትን ግርማ ሞገስ የሚሰልቡ ናቸው፡፡ እነርስሩም እንደሚከተሉት ናቸው፡፡

1

በሰላት ውስጥ መዞር የተጠላ ተግባር ነው ምክንያቱም ነቢዩ(ሰ∙ዐ∙ወ) በሰላት ውስጥ መዞርን (እየዞረ መመልከትን) አስመልክቶ ጥያቄ ሲቀርብላቸው ‹‹እርሱ ሰርቆት ነው(ሸይጧ የአላህ ባሪያ ከሰላቱ ይሰርቀዋል›› ብለዋል።(ቡኻሪ፡ 718)

2

በሠላት ውስጥ በእጆች፣ በፊት፣ ጣቶችን በማጣመርና በማንጫጫት መጫወት ይጠላል፡፡

ሰላት ውስጥ ፊትን ወይም እጅን እያነካኩ መጫወት ይጠላል።

3

አንድ ሰው፣ ልቡ በሽንት ሐሳብና በምግብ ክጃሎት ሐሳብ ልቡ ተጠምዶ ወደ ሠላት መግባቱ ይጠላል፡፡ ነገሩ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዳሉት ነው፡፡ ‹‹ምግብ ቀርቦ፣ ሁለቱ ቀሻሾች እየገፈተሩትም ሠላት የለም›› (ሙስሊም 560)