አንድ ሙስሊም ሐጅ ማድረግ የመቻል መገለጫዎች፡

አንድ ሙስሊም ሐጅ ማድረግ የመቻል መገለጫዎች፡


1

በራሱ ሐጅ ማድረግ መቻሉ፡ አንድ ሙስሊም፣ በቂ ገንዘብ ያለው ከሆነና ከተለመደው የጉዞ እንግልት በተጨማሪ ምንም ዓይነት እንግልት ሳይደርስበት በራሱ ወደ በይተል ሐራም መድረስ ከቻለ የግዴታን ሐጅ በራሱ የማድረግ ግዳጅ አለበት፡፡

2

በራሱ ሳይሆን በሌላ ሰው ሐጅን ማስፈፀም የሚችል መሆኑ፡ ዕድሜው የገፋ አዛውንት በመሆኑ ወይም ህመምተኛ በመሆኑ ምክንያት ሐጅ ማድረግ የማይችል፣ ነገር ግን እርሱን ወክሎ ሐጅ ሊያደርግለት የሚችልን ሰው የሚያገኝ ከሆነና እርሱን ወክሎ ሐጅ እንዲያደርግለት ወጪውን መሸፈን ከቻለ፣ የወኪሉን ወጭ ሸፍኖ ሐጅ የማስደረግ ግዴታ አለበት፡፡

3

በራሱም ሆነ በሌላ ሰው አማካይነት ሐጅ ማድረግ የማይችል፡ ይህ ዓይነቱ ሰው የማይችል እስከሆነ ድረስ ሐጅ የማድረግ ግዴታ የለበትም፡፡


ፍላጎቱን ከሚያሟላበትና የቤተሰቡን ወጪ ከሚሸፍንበት የሚተርፈው ሐጅ ሊያደርግበት የሚችል ምንም ዓይነት ገንዘብ የሌለው ሰው በምሳሌነት ይጠቀሳል፡፡

ሐጅ ማድረግ የሚያስችለው ገንዘብ ለማግኘት ገንዘብ የማሰባሰብ ግዴታ የለበትም፡፡ በቻለ ጊዜ ግን ሐጅ ግዳጅ ይሆንበታል፡፡


  • ሐጅ ለማድረግ የሚያበቃህ የሆነ በቂ ገንዘብና አካላዊ ብቃት
    • አዎን

      በራስህ ሐጅ ልታከናውን ግዴታ ይሆንብሃል፡፡

    • አይቻልም(በፍፁም)

      ሐጅ ለማድረግ በቂ ገንዘብ አለህ ነገር ግን ይድናል ተብሎ በማይከጀል ሕመም ምክንያት ሐጅ ለማድረግ የሚያስችል የአካል ብቃት የለህም፣አለያም በጣም ሸምግለሃል፡፡

      • አዎን

        በዚህን ጊዜ አንተን ወክሎ ሐጅ ለሚያደርግ ሰው ወጪውን የመሸፈን ግዴታ አለብህ፡፡

      • አይቻልም(በፍፁም)

        ከመሰረታዊ ፍላጎቶችህና በአንተ ስር ከሚተዳደሩ ሰዎች መሰረታዊ ወጪ የሚተርፍ የሆነና ሐጅ ለማድረግ የሚያስችልህ በቂ ገንዘብ ከሌለህ ሐጅ የማድረግ ግዳጅ የለብህም፡፡ ሐጅ ለማድረግ ገንዘብ ማስባሰብም አይጠበቅብህም፡፡