ሸሪዓዊው አደን የሚፈቅደው፣ ስጋቸው የሚፈቀድ፣ ነገር ግን እነርሱን በቁጥጥር ስር አውሎ መባረክና ማረድ የማይመች የሆኑ እንስሳትን ነው፡፡ ለምሳሌ፡ ስጋ በሊታ ከሆኑት በጫካና በዱር የሚገኙ አዕዋፍ፣ እንዲሁም ሚዳቋ፣ ጥንቸልና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
ለአደን መስፈርቶች አሉት፡፡ ከነርሱም መካከል፡
1አዳኙ፣ ጤናማ አዕምሮ ያለው፣ አደንን አስቦ የወጣ፣ ሙስሊም አለያም ከመጽሐፍት ባለቤት የሆነ መሆን አለበት፡፡ ጣዖት አምላኪ ወይም አዕምሮን የሳተ ሰው ያደነው አይፈቀድም፡፡ 2እንሰሳው በመበርገግና ከሰው በመራቁ ምክንያት ተባሮ ሊያዝና ሊታረድ የማይችል መሆን አለበት፡፡ እንደ ዶሮ፣ ፍየልና በግ፣ እንዲሁም ከብት አይነት ከሆነ ማደን አይቻልም፡፡ 3እንሰሳው የሚገደልበት መሳሪያ እንደ ቀስት፣ ጥይትና የመሳሰሉ መሳሪያዎች ዓይነት በስለቱ የሚገድል መሆን አለበት፡፡ እንደ ድንጋይና መሰል በክብደቱየሚገድል ዓይነት፣ ሰውዬው እንሰሳው ከመሞቱ በፊት ደርሶ የሚባርከውና የሚያርደው ካልሆነ በስተቀር መመገቡ አይፈቀድም፡፡ 4ማደኛ መሳሪያውን ከመተኮሱ ወይም ከመልቀቁ በፊት፣ ‹‹ቢስሚላህ›› በማለት የአላህን ስም ማውሳት አለበት፡፡ 5እንሰሳውን ወይንም በራሪውን ካደነው በኋላ ሳይሞት በሕይወት ካገኘው በማረድ ሐላል ሊያደርገው ይገባል፡፡ 6ለመብላት ካልሆነ በስተቀር እንሰሳትን ማደን እርም ነው፡፡ ያደኑትን ላይበሉ፣ ለመዝናናትና ለሌላ ጥቅማ ጥቅም እንሰሳትን ማደን ክልክል ነው፡፡ ![]() |